አልኮል ስንጎነጭ፣ ሽንት ያመላልሰናል፤ አልኮል መጠጦች በብዛት የሚያሸኑን ለምንድነው? ጤና ላይ ችግር አለው? መቀነስስ እንችላለን?

አልኮል መጠጥ አሻኚ( diuretic) ነው፤ ማለትም አልኮል ስንጠጣ ከጠጣነው በላይ ያሸናናል፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት አልኮል አርጊኒን ቫሶፕረሲን( arginine vasopressin) ወይም ፀረ-አሸኚ ሆርሞን( anti-diuretic hormone (ADH)) ላይ ጣልቃ በመግባት ስለሚጨቁነው ነው፤ የዚህ ሆርሞን ስራ ኩላሊታችን ውኃን ወደ ደም እንዲመለስ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን በአልኮል ተፅእኖ ምክንያት በሰውነታችን ውስጥ የሚዘዋወረው ውኃ በኩላሊት አማካኝነት ወደ ደም በመመለስ ፋንታ በሽንት መልክ እንዲወጣ ይገደዳል፡፡
አልኮል መጠጥ አሻኚ( diuretic) ነው፤ ማለትም አልኮል ስንጠጣ ከጠጣነው በላይ ያሸናናል

አልኮል በተጎነጨን ቁጥር ሂደቱ እየተደመረ የምንሸናውም እየጨመረ ይሄዳል፤ ይህ ሂደት በሰውነት ላይ የፈሳሽ ብክነት( dehydration) እንዲፈጠር ያደርጋል፤ ምክንያቱም ውኃ ወደ ደም እንዲመለስ፣ ኩላሊት ላይ ተፅእኖ የሚፈጥረው ሆርሞን(ADH) ተጨቁኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ አልኮል የሽንት ፊኛን የማነሳሳት ባሕሪ አለው፤ በመሆኑም በቂ የሆነ ሽንት እንኳን በፊኛችን ባይኖረንም የሽንት መጣሁ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
አልኮል ሽንት እንኳን በፊኛችን ባይኖረንም የሽንት መጣሁ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

ሽንት የሚመረትበት አንፃረ ጊዜ ምን ያክል ነው?

በጤናማ ጊዜያት አንድ ሰው በሰዓት ከ60-80 ሚሊ ሊትር ሽንት ያመርታል፤ ነገር ግን አልኮል ስንጎነጭ ተጨማሪ 120 ሚሊ ሊትር ሽንት እንዲመረት ያደርጋል፤ ዝቅተኛ የውኃ መጠን ሰውነታችን እያለው ወይም ተጠምተን እያለ በላዩ ላይ አልኮል መጠጣት፣ ሰውነታችን ውስጥ ሊቆይ ይገባ የነበረውን ውኃ በሽንት መልክ እንዲወጣ ስለሚደረግ፣ የውኃ ድርቀት( dehydrated) ሁኔታ ይፈጠርብናል፡፡ በአልኮል መጠጥ ላይ በተጨማሪ የማላብና የማስመለስ ሁኔታ ካለ የምናጣው የሰውነት ፈሳሽ በእጅጉ ይጨምራል፡፡ የሰውነት ፈሳሽ ብክነትን ለመቀነስ አልኮል ከመጠጣት በፊት ውኃ በመጠጣት በጥሩ ይዘት( hydrated) ላይ መገኘት ጥቅም ያለው ቢሆንም ዞሮ ዞሮ አልኮል ስንጎነጭ የሽንት ሂደት እንዲወጣ ስለሚያደርገው አልኮል ላይ ከቆየን የሰውነት ውኃ ድርቀት መፈጠሩ አይቀርም፡፡
በጤናማ ጊዜያት አንድ ሰው በሰዓት ከ60-80 ሚሊ ሊትር ሽንት ያመርታል፤ ነገር ግን አልኮል ስንጎነጭ ተጨማሪ 120 ሚሊ ሊትር ሽንት እንዲመረት ያደርጋል

ይህንን ሁኔታ መቀነስ እንችላለን ወይ?

አልኮል ስንጎነጭ ጎን ለጎን ውኃ ወይም ለስላሳ መጠጦች መጠጣት በአልኮል አማካኝነት የምናጣውን የሰውነት ፈሳሽ በግማሽ ሊቀንስ ይችላል፤ የሰውነት ፈሳሽ መጠን ከተጠበቀ በቀጣይ ቀን የሚፈጠረው የሃንጎቨር ሁኔታም ሊቀንስ ይችላል፤ ነገር ግን ምንም እንኳን አልኮል በብዛት እየተጎነጨን ጎን ለጎን ውኃ መጠጣታችንን ብንቀጥልም የሰውነት ፈሳሽ ብክነት ማጋጠሙ አይቀርም፤ ምክንያቱም ኩላሊት ውኃውን ወደ ደምና አባላተ-አካላት ለመመለስ በአልኮል ተፅእኖ ስለሚደርስበት በቆይታ ጊዜ የሰውነት ውኃ በሽንት መባከኑ አይቀርም፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ያለውኃ አልኮል መጠጥ ብቻ እየጠጣ ብዙ ሊቆይ አይችልም፤ ምክንያቱም የሰውነት ፈሳሽ በሙሉ በመባከን ሊሞት ይችላልና፡፡
የአልኮል ተፅእኖን ለመቀነስ እንዲሁም ሃንግኦቨር ለመቀነስ በቀጣይ ቀን ውኃ በብዛት መጠጣት በእጅጉ ሊረዳ ይችላል፡፡

ለወዳጆችዎም ያጋሩ!

ምንጭ:- www.survival101.info

Comments

Popular posts from this blog

በዓለም ላይ ከሚገኙት ወደ 3000 የሚጠጉ የእባብ ዝርያዎች 600 የሚሆኑት መርዛማ ናቸው፤ የተነደፍነው በመርዛማ እባቦች መሆኑን እንዴት እንለያለን? ምንስ ማድረግ አለብን?

ጤናአዳም ብዙ የጤና በረከቶች እንዳሉት ሁሉ መጠኑ ሲበዛ ፅንስ እስከማስወረድ የሚደርስ አደገኛነት እንዳለው ያውቃሉ?

የስኳር በሽታ እንዴት ይፈጠራል? መቆጣጠሪያ መንገዱስ እንዴት ነው?