ጤናአዳም ብዙ የጤና በረከቶች እንዳሉት ሁሉ መጠኑ ሲበዛ ፅንስ እስከማስወረድ የሚደርስ አደገኛነት እንዳለው ያውቃሉ?
በሳይንሳዊ ስሙ ሩታ ካሌፔንሲስ(Ruta chalepensis) እየተባለ የሚጠራው ጤናአዳም አገራችንን ጨምሮ በሜዲትራንያንና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ይበቅላል፤ ሩታ የሚለው ስም የጥንት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም እጅግ መራራ ወይም ደስ የማያሰኝ ማለት ነው፡፡ የተክሉ መራራነት የመጣው በውስጡ ከሚገኘው ሩትን(rutin) ከተባለ ውሁድ ነው፡፡ በሳይንሳዊ ስሙ ላይ ካሌፔንሲስ የሚለው ስም የተሰጠው ከጥንቷ የሶርያ መንደር ካሌፕ( Chalep) ነው፤ ዛሬ ላይ ይህ አካባቢ ሃሌብ( Haleb) ወይም አሌፖ( Aleppo) የሚባለው ነው፡፡ በሳይንሳዊ ስሙ ላይ ካሌፔንሲስ የሚለው ስም የተሰጠው ከጥንቷ የሶርያ መንደር ካሌፕ( Chalep) ነው ከጤናዳም ስር ነጥሮ የሚወጣው የኬሚካል ውህድ አልካሎይድ የሆኑ ክሎሮዶን( chaloridone)፣ ስኪሚያኒን( chaloridone)፣ ኩኩሳግኒንና ግሬቮሊን( kokusaginine and graveoline) ከኩማሪንስ ጋር ሩታልፒኒን( rutalpinin)፣ ካሌፒን( chalepin) እና ካሌፔንሲን( chalepensin) ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የባሕል ሕክምና ጤናአዳም ለሆድ ሕመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጆሮ፣ ለልብ ሕመም፣ ለኪንታሮት፣ ለኢንፍልዌንዛና ከአንጀት መታወክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ የደረቀው ፍሬ ከተፈጨ በኋላ ተፈልቶ በመጠጣት ለተቅማጥ ሕክምና ሲውል፣ ቅጠሉ ከተከተከተ በኋላ በውኃ ተደርጎ ለሕፃናት ሆድ ሕመም ይሰጣል፤ ተክሉ ተድጦ ሲልም ደግሞ ለኪንታሮት በሽታ ይወሰዳል፡፡ በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ደግሞ ከተክሉ ተዘፍዝፎ የሚገኘው ፈሳሽ ለጉንፋን፣ ለጆሮ ሕመምና ለአንጀት መታወክ ይወሰዳል፡፡ የጤናዳም ሽታ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ሰዎች ጊንጦችን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይጠቀሙታል፡፡ በአልጀ...
Comments
Post a Comment