Posts

S. SUDAN’S KIIR TO ATTEND IGAD’S EXTRAORDINARY SUMMIT IN ETHIOPIA

Image
(Sudan Tribun)- South Sudan president Salva Kiir will attend the upcoming extraordinary summit organised by the intergovernmental authority on development (IGAD), the regional bloc which mediated the 2015 peace agreement to end the devastating conflict in the young nation. A presidential aide said the South Sudan leader would himself attend the summit if no important matters required his attention at home. “This is an important meeting of heads of state of the IGAD member countries. It is being specifically convened to discuss the current situation in the country, which is an encouraging and important initiative”, Tor Deng Mawien, the presidential advisor on decentralisation and intergovernmental linkage said Wednesday. He said IGAD has a role in persuading armed and non-political forces to join the national dialogue. He stressing that a home-grown peace deal from the dialogue will be sustainable, inclusive and grounded on the full respect of the ratified international human...

በዓለም ላይ ከሚገኙት ወደ 3000 የሚጠጉ የእባብ ዝርያዎች 600 የሚሆኑት መርዛማ ናቸው፤ የተነደፍነው በመርዛማ እባቦች መሆኑን እንዴት እንለያለን? ምንስ ማድረግ አለብን?

Image
በዓለም ላይ ከሚገኙት ወደ 3000 የሚጠጉ የእባብ ዝርያዎች 600 የሚሆኑት መርዛማ ናቸው፤ 200 የሚሆኑት ደግሞ ለህክምና ወይም ለመድኃኒት አግልግሎት የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ መርዛማ እባቦችን ለመለየት ይሄ ነው የሚባል መንገድ ለመከተል ይከብዳል፤ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የመለያ መንገዶች የቅርብ ምልከታን የሚፈልጉ በመሆኑ ነው፤ ስለዚህ ከእባቦች ስጋትና ጥቃት ነፃ ልንሆን የምንችለው ከእነርሱ በመራቅ ነው፡፡ የአንድ መርዛማ እባብ ንድፊያ የተለያዩ የሰውነት አካላት ላይ በፍጥነት ጉዳት ማድረስ ይጀምራል፤ እንደ ሳንባ፣ ልብ፣ የማዕከላዊ ነርቭ ስርዓት፣ የቀይ ደም ሕዋሶችና የጡንቻ ስርዓት ያሉት በቀጥታ ጉዳት ከሚገጥማቸው የሰውነት አካላት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በመሆኑም የእባብ መርዝ የነርቭ ስርዓትን የሚያጠቃ(neurotoxic)፣ በደም ሕዋሶች ላይ ጉዳት የሚያደርስ(haemotoxic)፣ ልብን የሚጎዳ(cardiotoxic) እና በጡንቻዎች ላይ እንከን የሚፈጥር(myotoxic) ተብሎ ሊከፈል ይችላል፤ በዚህ ምክንያት የሚሰጠውም የማርከሻ ሕክምና የተለያየ ነው፤ ይህ በመሆኑም በሕክምናው ስኬታማ ለመሆን በምን ዓይነት እባብ እንደተነደፍን ማወቅ አለብን፡፡ በዓለማችን ላይ በአመት ወደ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በእባብ ይነደፋሉ፤ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 100 ሺህ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጣሉ በዓለማችን ላይ በአመት ወደ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በእባብ ይነደፋሉ፤ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 100 ሺህ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጣሉ፤ 5 መቶ ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ቋሚ የአካል ጉዳት ይገጥማቸዋል፤ የመርዛማ እባብ ንድፊያ ማርከሻውን ካላገኘ ለሞት የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ እባቦች በአማካኝ በሳምንት አንድ ጊዜ ይመገባሉ፤ ከተመገቡ በኋላ እንዲሁም ቆዳቸውን በሚሸልቱበት ጊዜ...

ጤናአዳም ብዙ የጤና በረከቶች እንዳሉት ሁሉ መጠኑ ሲበዛ ፅንስ እስከማስወረድ የሚደርስ አደገኛነት እንዳለው ያውቃሉ?

Image
በሳይንሳዊ ስሙ ሩታ ካሌፔንሲስ(Ruta chalepensis) እየተባለ የሚጠራው ጤናአዳም አገራችንን ጨምሮ በሜዲትራንያንና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ይበቅላል፤ ሩታ የሚለው ስም የጥንት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም እጅግ መራራ ወይም ደስ የማያሰኝ ማለት ነው፡፡ የተክሉ መራራነት የመጣው በውስጡ ከሚገኘው ሩትን(rutin) ከተባለ  ውሁድ ነው፡፡ በሳይንሳዊ ስሙ ላይ ካሌፔንሲስ የሚለው ስም የተሰጠው ከጥንቷ የሶርያ መንደር ካሌፕ( Chalep) ነው፤ ዛሬ ላይ ይህ አካባቢ ሃሌብ( Haleb) ወይም አሌፖ( Aleppo) የሚባለው ነው፡፡ በሳይንሳዊ ስሙ ላይ ካሌፔንሲስ የሚለው ስም የተሰጠው ከጥንቷ የሶርያ መንደር ካሌፕ( Chalep) ነው ከጤናዳም ስር ነጥሮ የሚወጣው የኬሚካል ውህድ አልካሎይድ የሆኑ ክሎሮዶን( chaloridone)፣ ስኪሚያኒን( chaloridone)፣ ኩኩሳግኒንና ግሬቮሊን( kokusaginine and graveoline) ከኩማሪንስ ጋር ሩታልፒኒን( rutalpinin)፣ ካሌፒን( chalepin) እና ካሌፔንሲን( chalepensin) ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የባሕል ሕክምና ጤናአዳም ለሆድ ሕመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጆሮ፣ ለልብ ሕመም፣ ለኪንታሮት፣ ለኢንፍልዌንዛና ከአንጀት መታወክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ የደረቀው ፍሬ ከተፈጨ በኋላ ተፈልቶ በመጠጣት ለተቅማጥ ሕክምና ሲውል፣ ቅጠሉ ከተከተከተ በኋላ በውኃ  ተደርጎ ለሕፃናት ሆድ ሕመም ይሰጣል፤ ተክሉ ተድጦ ሲልም ደግሞ ለኪንታሮት በሽታ ይወሰዳል፡፡ በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ደግሞ ከተክሉ ተዘፍዝፎ የሚገኘው ፈሳሽ ለጉንፋን፣ ለጆሮ ሕመምና ለአንጀት መታወክ ይወሰዳል፡፡ የጤናዳም ሽታ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ሰዎች ጊንጦችን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይጠቀሙታል፡፡ በአልጀ...

የስኳር በሽታ እንዴት ይፈጠራል? መቆጣጠሪያ መንገዱስ እንዴት ነው?

Image
የስኳር በሽታ፣ ጉሉኮስ፣ ግላይኮጅን፣ ግሉካጎንና ኢንሱሊን ያላቸው ግንኙነት ግሉኮስ(glucose) ግሉኮስ ቀለል ያለ የስኳር ውቅር ነው፤ አቻ የሞለኪል ቀመሩ (C 6 H 12 O 6 ) ሲሆን በእንስሳት ደም ውስጥ የሚዘዋወር ለሕዋሶች አስፈላጊ የሆነ የኃይል ምንጭ ነው፤ ግሉኮስን የሚሰሩት እፅዋት ናቸው፤ እፅዋት ውኃ እና ካርቦን ዳይኦክሳይድን ከፀሐይ ብርሃን ጋር በማስተፃመር ነው የሚያመርቱት፤ ግሉኮስ በእፅዋት ውስጥ በስታርች( starch) መልክ የሚቀመጥ ሲሆን በእንስሳት ውስጥ ደግሞ ግላይኮጅን( glycogen) በሚባል ግን’ብ መልክ ይቀመጣል፡፡ ኢንሱሊን ምንድነው? በሰውነታችን ውስጥ የሚሰራው ስራ ምንድነው? ምግብ ከተመገብን በኋላ፣ ከምግቡ የምናገኘው ግሉኮስ(glucose) በትንሹ አንጀት በኩል አድርጎ ወደ ደም ይቀላቀላል፤ ይህም በመሆኑ ምግብ ከተመገብን በኋላ የግሉኮስ መጠን በደማችን ውስጥ ይጨምራል፤ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ሕዋሶች በደም ውስጥ የሚገኘውን ግሉኮስ ለተለያዩ ስራቸው እንደ ኃይል ይጠቀሙታል፤ ይህ ሂደት በደም ውስጥ የሚገኝ የግሉኮስ መጠን ክምችት እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ሕዋሶቻችን የሚጠበቅባቸውን ተግባራት በሚገባ ለማከናወን በደም ውስጥ የሚገኘው የግሉኮስ መጠን ሳይዋዥቅ በሆነ መጠን ላይ ሚዛኑን ጠብቆ እንዲቆይ ያስፈልጋል፤ ሚዛኑን ጠብቆ በሆነ ልኬት ላይ እንዲቆይ ግን የሆነ መቆጣጠሪያ መንገድ ያስፈልገዋል፤ አለዚያ ጉሉኮስ በደም ውስጥ ወይ በጣም መብዛት ወይም ማነስ ያጋጥማል፡፡ኢንሱሊን የዚህን ቁጥጥር ስራ የሚሰራ ቅመም ወይም ሆርሞን ነው፡፡ ኢንሱሊን ጉበት ጉበት በደም ውስጥ የሚገኘውን የግሉኮስ መጠን ለመቆጣጠር የሚረዳ ሚና አለው፤ ከጉበት በተጨማሪም ቆሽታችን(pancreas) በዚህ ተግባር ላይ ዋና ተሳታፊ ነው...